GAC Spiritual Media | ጂኤሲ መንፈሳዊ ሚዲያ

Gospel to All Creation is a Christ-centered ministry dedicated to preaching the pure Gospel of Jesus Christ to all nations, tribes, and generations.

This channel exists to:
• 🔥 Proclaim the saving power of Jesus Christ
• 📖 Teach sound, Bible-based doctrine
• 🙏 Lead people into prayer, repentance, and spiritual renewal
• 🌍 Reach the nations with the Gospel through preaching, worship, and teaching

Through powerful sermons, live prayers, worship moments, Bible teachings, and special revival messages, we believe God is touching lives, healing hearts, breaking chains, and drawing people closer to Him.

Whether you are a new believer, a growing Christian, or a servant of God, this channel is here to strengthen your faith, ignite your hunger for God, and equip you for victorious Christian living.
-------------------------------------------------------------
For more contact an official email:- gtacichurch@gmail.com


GAC Spiritual Media | ጂኤሲ መንፈሳዊ ሚዲያ

አዲስ ፊልም ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ

https://youtu.be/IyCNTysSOlo

1 year ago | [YT] | 0

GAC Spiritual Media | ጂኤሲ መንፈሳዊ ሚዲያ

ኢየሱስ አማላጅ ወይስ ፈራጅ?
ኢየሱስ አማላጅ ነው? መልሱ አወ ከሆነ ከማን ጋር ነው ሚያማልደው? እሱ አምላክ ነው አምላክ ከሆን ደግሞ ፈራጅ እንጂ አማላጅ ሊሆን አይችልም።
ብዙ ጊዜ አንዳንድ የወንጌላውያን አማኞችም ሆነ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ወንድሞቻን ጭምር እነዚህ ጥያቄዎች ይነሳሉ፣ ታዲያ ይህ ብዥታ ከምን የመጣ ነው።
በመስቀል ለምታምኑ ወገኖች፣ ኢየሱስ አማላጅ ነው ካላችሁ ከማን ያማልዳል ለምትሉ አንድ ጥያቄ ኣለኝ። እርሱ አምላክ ከሆነ በመስቀል ለምን ሞተ? አምላክ ይሞታል እንዴ? ኢየሱስን ሲገርፉት ነበር አምላክን መግረፍ ይቻላል እንዴ? ይህንን ጥያቄ መመለስ ግድ ይላል።
በብዙዎች ዘንድ ይህ ብዥታ ሊፈጠር የቻለው ምክንያት ኢየሱስ ማን እንደሆነ ካለማወቅ ወይም ስለ ክርስቶስ ማንነት ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ ነው።
ኢየሱስ ማነው?
ኢየሱስ ፍጹም ሰው እና ፍጹም አምላክ ነው።
ሰው የሆነው ኢየሱስ።
================
ኢየሱስ በሉቃ 2 እና ኢሳ 53 በተጻፈው መሰረት ። የሰው ልጅ በአዳም ምክንያት በሀጢያት መውደቁን ተከትሎ የሰውን ልጅ ለማዳን ስጋ ለብሷል። ይህ ስጋን የለበሰው ማንነቱ ፍጹም ሰው ይባላል። ፍጹም ሰው ሲባል የሚባላ፣ የሚጠጣ፣ እንደ ሰው ልጅ የሚደክም፣ የሚገረፍ፣ የሚሰቀል፣ ብትችል አባቴ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ብሎ የሚጸልይ ማለት ነው። ኢየሱስ በአዳም ምክንያት በሀጢያጥ የወደቀውን የሰው ልጅ በመስቀል ላይ የሀጢያትን ዋጋ የከፈለው በዚህ በለበሰው ሰው በሆነው ማንነቱ እንጂ በአምላክነቱ አይደለም። ስለዚህ ኢየሱስ አማላጅ ነው ሲባል ሌላኛው አቻ ትርጉም ማስታረቅ ሲሆን በምድር ላይ አምላክንና ሰውን በገዛ ሰውነቱ የሀጢያትን ዋጋ በመስቀል የከፈለውን ሂደት አማለደ ወይም አስታረቀ ይባላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀው ወይም ያማለደው በገዛ ስጋው በመስቀል ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በከፈለው ዋጋ እንጂ በየቀኑ የአልም ህዝብ ሀጢያትን በሰራ ጊዜ ሁሉ እባክህ እባክህ ማለቱ አይደለም። ኢየሱስ ሰው በሆነው ማንነቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሏል ያ በመስቀሉ ላይ የሰራው ስራ የማማለድ ስራ ይባላል።ይህ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ የሰራው የማማለድ ስራ ዛሬም ነገም ዳግም እስኪመጣ ይሰራል።
አምላክ የሆነው ኢየሱስ
ኢየሱስ ሰው ብቻ ሳይሆን አምላክም ነው። አንዳንድ ቤተ እምነት አማኞች ኢየሱስ ፈራጅ ነው ይላሉ ይህን ማለታቸው ልክ ነው ነገር ግን ኢየሱስ ፈራጅ የሆነው በአምላክነቱ እንጂ በሰውነቱ አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ በአማልክነቱ ይፈርዳል የሚፈርደው ደግሞ ዳግም ሲመጣ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ፈራጅ ሆነ አልነበረም የመጣው አማላጅ ሆኖ እንጂ በሌላ አባባል ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣው ስጋ ለብሶ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው ። ምንም እንኳን ኢየሱስ ስጋ ለብሶ ፍጹም ሰው ቢሆንም ፍጽም አምላክም ነው። ኢየሱስ በአምላክነቱ ሀጢያትን አስተሰረየ፣ ሙታንን አስነሳ፣ ድንቅንና ተዓምራትን አደረገ፣ ተሰወረ። እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ነገሮች በሙሉ አምላክ እንጂ ሰው ማድረግ አይችልም። በሌላ መንገድ አገላለጽ አምላክ ብቻ ማድረግ የሚችላቸው ነገሮች ናቸው።
ማጠቃለያ
ኢየሱስ ፍጹም ሰው እና ፍጹም አምላክ መሆኑን አንድ ሰው ካልተረዳ ስለ ኢየሱስ አማላጅነትም ሆነ ፈራጅነት ይምታታበታል።
ስለዚህ ኢየሱስ አማላጅ የሆነው ስጋ በለበሰው እና ፍጹም ሰው በሆነው ማንነቱ እንጂ በአምላክነቱ አይደለም።
ኢየሱስ ፈራጅ የሆነው መለኮት በሆነው አምላክነቱ እንጂ ስጋ በለበሰው ሰውነቱ አይደለም።
ኢየሱስ አማላጅ ነው ያ ሰው በሆነ ማንነቱ ነው።
ኢየሱስ ፈራጅ ነው ያ ደግሞ አምላክ በሆነ ማንነቱ ነው።
ምክንያቱም ኢየሱስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ስለሆነ። መልካም እሁድ።

4 years ago | [YT] | 5