Zola Media ዞላ ሚዲያ

እንኳን ወደ 🛑 ዞላ ሚዲያ Zola Media በሰላም መጣችሁ , በዚህ ሚዲያ/channel የህክምና ትምህርቶችን, ስለ ጤናማ ህይወት, ዩቲዪብ አልጎሪዝም: ስፖርት እና ሌሎች ጠቃሚ ቪዲዮችን ያገኙበታል።
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
Subscribe 🔔
Welcome to 🛑 Zola Media, in this channel you will get plenty of Medical and health related knowledges, Lectures, sexual and reproductive health, lifestyle principles and secrets, and exercise.

Founded by : - Mr. Zelalem Mekuria ; University Lecturer (BSC, Registered Nurse, MSC In Medical Anatomy)

Anatomy Lecturer
Registered Nurse


ፌስቡክ ገጽ ሊንክ Facebook Link
www.facebook.com/share/16WcwhEv7y/

ቴሌግራም
t.me/zolabtube

WhatsApp number +971501185963 or telegram - +251928458302



Zola Media ዞላ ሚዲያ

ድምፅ አልባው ገዳይ ...👇
silent killer በመባል የሚታወቀው የደም ግፊት(hypertension ) በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለ ችግር ሆኗል። በአሁኑ ሰዓት የበሽታው ስርጭት በአለም አቀፍ ደረጃ 31.5 % በኢትዮጵያ ከ 21.8 % በላይ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።

የደም ግፊት በተለምዶ “ደም ብዛት” የሚባለው ደም በደም ወሳጅ ቧንቧዎች(Arteries) ላይ የሚያሳድረው ግፊት መጠን ማለት ነው። የደም ግፊት ከልብ ምት የሚመነጭ እና ደም በሰውነት እንዲዘዋወር የሚረዳ የግፊት ሀይል ነው። የደም ግፊት ከሚገባው በላይ ሲጨምር የደም ቧምቧዎችን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። ይህም የደም ብዛት ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት (hypertension ወይም high blood pressure) ይባላል። በተለያዩ ጊዜያት ቢያንስ ሁለት ጊዜ ተለክቶ የላይኛው ግፊት (systolic) 130mmHg በላይ ወይም የታችኛው ግፊት (diastolic) 80 mmHg በላይ ሲሆን ነው፡፡ የላይኛው ወይም የታችኛው ከመጠን በላይ ከሆነ ደም ግፊት አለ ማለት ይቻላል፡፡ የግድ ሁለቱም ከፍተኛ እንዲሆን አይጠበቅም፡፡ ትክክለኛው የደም ግፊት መጠን የላይኛው ከ90-140 ሲሆን የታችኛው ከ60-90 ነው፡፡ ነገር ግን ከ 130 በ80 በታች ቢሆን ለጤንነት የተሻለ ነው፡፡

ለምሳሌ የደም ግፊቱ 125/80 የሆነ ሰው:-

# የላይኛው ሲስቶሊክ/systolic የደም ግፊት የሚባለው ፦ልብ ደምን ወደ ሰውነታችን በደም ቅዳ ለመርጨት በሚኮማተርበት ግዜ የሚኖረው የግፊት መጠን ሲሆን

# የታችኛው ዲያስቶሊክ/diastolic የደም ግፊት የምንለው ፦ልብ ደም ለመሙላት ዘና(relax) በሚያደርግበት ግዜ የሚፈጠር የግፊት መጠን ነው

የከፍተኛ የደም ግፊት መንስዔዎች ወይንም ምክንያቶች

📌 የእድሜ መግፋት ፦በተለይም እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶችና ከ55 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች የመያዝ ዕድላቸው ይጨምራል።

📌 በበሽታው የተያዘ ሰው በቤተሰብ ውስጥ መኖር

📌 ከመጠን ያለፈ ውፍረትና የሰውነት ክብደት

📌 የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ

📌 ሲጋራ ማጨስ

📌 የአልኮል መጠጣት

📌 ከመጠን ያለፈ ጭንቀት

📌 ጨው የበዛባቸውን ምግቦች መመገብ

📌 አብዛኛውን ጊዜ በማይታወቅ ምክንያት ይከሰታል ለምሳሌ:- በአካባቢያዊና በዘር ውርስ ምክንያቶች(Environmental and genetic factors) ይመጣል ተብሎ ይታመናል።



የደም ግፊት በሽታ ምልክቶች

👉 የከፍተኛ ግፊት በሽታ አብዛኛውን ግዜ ምልክት አያሳይም(ለዚህም አደል ዝምተኛው ገዳይ የተባለው the silent killer) ስለዚህ ያለን ብቸኛው አማራጭ የክትትል ምርመራ ማድረግ ነው። ነገር ግን ግፊታችን ከመጠን በላይ ሲጨምር የሚከተሉትን ምልክቶች ልናይ እንችላለን

📌 ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት

📌 የእይታ ችግር

📌 የድካም ስሜት

📌 የደረት ህመም

📌 ለመተንፈስ መቸገር

📌 የልብ ምት መዛባት

📌 ልባችን ሲመታ ለራሳችን መታወቅ

📌 ራስን መሳት ወይም የሰውነት መንዘፍዘፍ

📌 የሰውነት መስነፍ ወይም መደንዘዝ

📌 ለማወራት መቸገር

📌 ማስታወክና ማቅለሽለሽ

📌 ደም የቀላቀለ ሽንት

የከፍተኛ የደም ግፊት መዘዞች

📌 በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስ ችግር(Stroke የሚባለው) ወይም ወደ ጭንቅላት የሚሄደው ደም መቀነስ / መቋረጥ

📌 የልብ ድካም

📌 ወደ ልብ ጡንቻዎች ደም የሚያዘዋውሩ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች መጎዳት( Coronary Heart Disease)


📌 የኩላሊት በሽታ

📌 የደም የቧምቧዎች በሽታ (Peripheral Arterial Diseases)


የደም ግፊትን ለመከላከልና ብሎም ለማከም መከተል ያለብን የአኗኗር ዘይቤዎች

📌 ጨው የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብና የገበታ ጨው አጠቃቀማችንን መመጠን ይህም ሲባል በቀን ከአንድ የሻይ ማንኪያ ያልበለጠ ወይም ደግሞ ከ 2 gm ያልበለጠ መጠቀም

📌 አትክልትና ፍራፍሬ፤አነስተኛ ቅባት ያላቸውን የእንስሳት ውጤቶችን፣ጥራጥሬ ፣የአትክልት ዘይቶችን ማዘውተር የሚከር ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ጣፋጭ መጠጦችንና ምግቦች እንዲሁም ቅባት የሚበዛባቸውን ምግቦች አለማዘውተር ይመከራል

📌 ከአልኮል ነክ መጠጦችን አለመጠቀም

📌 ሲጋራና ሌሎች የትንባሆ ውጤቶችን አለማጨስ

📌 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ (ቢያንስ በቀን ለ 40 ደቂቃ ፤በሳምንት ከ5-7 ግዜ መካከለኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ለምሳሌ እንደ ርምጃ ፣ዋና፣ሳይክል መንዳት፣ሶምሶማ የመሳሰሉትን

📌 የሰውነትን ክብደት መቀነስና ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖረን ማድረግ

ስለከፍተኛ የደም ግፊት የተሳሳቱ አመለካከቶች

📌 ወፍራምና ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ላይ ብቻ የሚከሰት አድርጎ ማሰብ

📌 የሀብታም በሽታ ነው ብሎ ማመን

📌 ምልክት ካላሳየ በቀር በሽታው የለብኝም ብሎ ማመን

📌 በቤተሰብ ውስጥ በበሽታው የተያዘ ሰው ስለሌለ ብቻ እኔ ላይ አይኖርም ብሎ ማመን

📌 በእርግማን የመጣ በሽታ አድርጎ ማመን

📌 እድሜያቸው የገፉ ሰዎች ላይ ብቻ የሚከሰት አድርጎ መቁጠር

📌 የባህል ህክምና ( ለምሳሌ ፦የግብጦ አረቄ ፣ ሞሪንጋ የመሳሰሉት ) ፈዋሽ አድርጎ መቁጠር

📌 ውፍረትንና ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደትን ጤናማ አድርጎ መቁጠር

📌 የገበታ ጨውን ብቸኛው የጨው ምንጭ አድርጎ መቁጠርና መሰል አጓጉል አስተሳሰቦችን ልናስወግድ ይገባል



ስለ silent killer ድምፅ አልባው ደም ግፊት በሽታ በአጭሩ ይሄንን ይመስላል

ያላችሁን ጥያቄ አስተያየት comment አድርጉልን
ሰብስክራይብ እንዳይረሳ 🥰 like, share አድርጉት
አመሰግናለሁ🙏

1 week ago | [YT] | 11

Zola Media ዞላ ሚዲያ

Reaching to another milestone!
50K Subscribers 🎉🎆🎉 Thank you all my Families!❤🎉🎉🎉🎉

7 months ago | [YT] | 60