ሕግን ከሰሎሞን ጋር-Lexology with SOLOMON

በዚህ ቻናል ከአድማስ በሙሉ የተሰናዱ ይህ ቀረሽ የማይባሉ ሕግ ተኮር ማህበራዊ፥ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ህጋዊ ይዘቶቻቸዉን እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችንና እንዳስሣለን። ጠቃሚ የሆኑ ዶክመንተሪዎችን በአማረኛ ቋንቋ እየመለስን እናጋራችኋለን። ቤተሰባችን ይሁኑ፣ ለሌሎችም አድርሱ። ሀሳብና አስተያየታችሁን በሚከተለው ሊንክ ያስቀምጡ። docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeBgJx5k0o5U-PfoA…


ሕግን ከሰሎሞን ጋር-Lexology with SOLOMON

በባንክ ብር ልከው አበድረን፤ ያበደርነው ሰው ብድር አይደለም ብሎ ቢክደን ባንክ ያስተላለፍንበት የሀዋላ ወረቀት/ደረሰኝ ምን ጥቅም እንዳለው ያውቃሉ? የብድር ዉልን የተመለከተ የፍርድ ቤት ክርክር ላይ ምን ምን ጉዳዮች ላይ መጠንቀቅ እንደሚገባም ማወቅ ከፈለጉ በዚህ ሊንክ ይከተሉ። https://youtu.be/i1UTmxiJrFQ

2 years ago | [YT] | 9

ሕግን ከሰሎሞን ጋር-Lexology with SOLOMON

በየትኛውም የአለም ጫፍ ላይ ያለ ሰው፥ ወንጀል መስራቱ በማስረጃ ካልተረጋገጠ በስተቀር ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት አለው፡፡ ይህ መብት እጅግ መሰረታዊና ዳኝነትን ፈታኝ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ ነው። በኢትዮጲያ ዉስጥ በብዛት በሚባል ደረጃ የሕግ ባለሙያዎችም ከማህበረሰቡ ባልተለየ ሁኔታ አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሮ ሲያዝ ወይም ሲከሰስ ያን ድርጊት እንደፈጸመው ግምት የመውሰድ ችግር አለ። ይህ ሁኔታ ከማህበረሰቡ ባይቀረፍ እንኳን በሕግ ባለሙያዎች በኩል በእጅጉ መስተካከል ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው ምንም ያክል ክፉ ቢሆን ሰው ሊገድል ይችላል ብሎ ግምት መዉሰድ ተገቢ አይደለም፥ ይልቁንም ሰው አይደል እንደ ሰው ሊገድል አይችልም የሚል ሀሳብ መያዝ ይኖርብናል! ማስረጃዎች አሳማኝ ሲሆኑ ብቻ ተገቢዉን አስተማሪ ቅጣት ይቀጣል!

3 years ago | [YT] | 5