yakobjmillion@gmail.com


Yakob Million

ኢየሱሴ
Coming soon new video
የዮሐንስ ወንጌል 5
2፤ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።
…5፤ በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤
*ያ ብቸኛ ሰው መልአኩ መጥመቂያውን ሲያናውጠው ውሀው ውስጥ ቀድሞ ገብቶ እንዳይፈወስ ጉልበት የለው ወይ ደግሞ ተሸክሞ ወደ ውሃው የሚከተው ዘመድ እንኳን የለው
የዮሐንስ ወንጌል 5
6፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ፦ ልትድን ትወዳለህን? አለው።
7፤ ሰውዩም፦ ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል፡ ብሎ መለሰለት።
*የሌሎችን ፈውስ እያየ ለዘመናት በሌሎች የተቀደመ የመሰለው ለመፈወስ ወረፋ ሲጠብቅ የነበረ... ብቸኛ... ቆሞ ይራመዳል ብሎ ማን ገመተ? ራሱን ለመርዳት እንኳን መንቀሳቀስ እንዳይችል እግሩ የማይታዘዘው ምስኪን ይሄ ፍቅር የሆነ ጌታ በአድራሻው መጥቶ ፈወሰው።
የዮሐንስ ወንጌል 5
8፤ ኢየሱስ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፡ አለው።
*ከራሱ አልፎ አልጋውን ተሸክሞ እንዲሄድ አዘዘው የምስኪኖች ወዳጅ እውነተኛ ፍቅር ኢየሱስ!❤️

3 years ago | [YT] | 23