Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

Kun chaanaalii Kabir Sheek Najib Muhammad Rashid Donocho Nego Sayedalarifin Hadra (Ahlesuna Wal Jama'a Ash'iri Wa Maturidi Asufiya) yoo ta'u chaanaalii kana keessattis daandii Haq Laa Ilaha Illah Muhammad Rasulullah, kan waggoota 200 oliif Masjiida Donocho Nego durii Godina Jimmaa Guddittii fi addaan hin cinne. Muhaderaan karaa Haq Laa Ilaha Illallah Muhammad Rasulullah, kan dhaloota 3 as jiraate itti tamsaasaa jirrudha. Suufiyyaa, Menzumaa, Taslimaa Zikrii, Baaroo Abiyoo, Hadiisa, Ta'leem, Dua
ይህ የከቢር ሼኽ ነጂብ ሙሀመድረሺድ ዶኖቾነጎ ሰይደልአሪፊን ሀድራ(የአህለሱና ወልጀመአ አሻኢሪ ወማቱሪዲ አሱፊያ) ቻናል ሲሆን በዚህ ቻናል የሀቢቡሏህን መውሊድ ከ 200 አመት በላይ በታላቁ ጅማ ክፍለ ሀገር በሚገኘው ጥንታዊው የዶኖቾ ነጎ መስጂድ እስካሁን ሳይቆረጥ ሲከበር የመጣውን በ 3 አባት(ትውልድ) እዚህ የደረሰውን የሀቅ ላኢላሀ ኢለሏህ ሙሀመደን ረሱሉላህን መንገድ የምናሰተላልፍበት ቻናል ነው። ሙሀደራ የሱፊ፣መንዙማ ፣ተስሊማ ዚክር፣ ባሮ አቢዮ፣ሀዲስ ፣ታእሊም፣ዱአ


Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

"ያ ረሱሊዎ ኮቱ ነለላሊሜ " ምርጥ የሙሀመድ አሊዪ ባሮ መንዙማ ተጋበዙልን የነቢዬﷺ ጃለሎዎች የአቢዮ ሼከናሁሴን ወዳጆች ይህን ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ማሜን ፍቅራቹን ግለፁለት...

8 months ago | [YT] | 0

Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

Subscribe mohammedalye jundi youtube channel

8 months ago | [YT] | 0

Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

Allahumerham NurenaHussen Abiyo baroo @mohammedalye jundi you tube channel subscribe godhaa
https://youtu.be/PVHnFFofuZQ?si=a9uDq...

11 months ago | [YT] | 3

Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

#ሙሐረም_10
#ዓሹራእ

የፊታችን ቅዳሜ የዓሹራእ ዕለት ይባላል። ምድር ላይ በደል ኹሉ የወደመበት ቀን ነው። ሰይድና ሙሳ ከብዙ እንግልት በኋላ ጨቋኙን ፈርኦንን አንኮታኩተው የጣሉበት፣ ሕዝባቸውን ይዘው ውሃው እንደትልቅ ሕንጻ ቀጥ ብሎ ቆሞላቸው የተሻገሩበት ድንቅ ታሪካችን ነው።

ይህ ዕለት ሲነሳ ሌላኛው የሚታወሰው ታሪክ ልባችን በቁጭት ላይ ኾኖ የሚያስታውሰው የሰይዳችንን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የልጅ ልጅ የእመት ፋጢማ ልጅ ሰይድና ሑሰይንን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ከባድ ጽናት ነው።

በሙሐረም 10 61 ሂጅሪያ ሰይድና ሑሰይን ተበድለው፣ ታጋሽ ኾነው፣ በሐቅ ላይ ጸንተው ሸሒድ (ሕያው) የኾኑበት ዕለት ነው። በዚህ ቀን ከሰይድና ሑሰይን ዙህድን፣ ትዕግስትን፣ መስእዋትነትን የአህለል በይት ፍቅርን በልባችን እንዲገባ የምንመኝበት ቀን ነው።

ኢማም ገዛሊይ (ቁዲሰ ሲረሁ) እንዲህ ይላሉ፦ « የኢኽላስ (ለአላህ የሚደረግ ቅንነት) ትልቁ ግቡ አንድ ባርያ ለአላህ ብቻ ብሎ መስራቱ ነው፤ ሰውነቱ ቢቆራረጥ እንኳን።» ይህን በዓሹራእ ዕለት ያደረገው ሑሰይን ነው።

ሰይድና ኢብን ዐረቢ (ቁዲሰ ሲረሁ) ፉቱሐት አልመኪያ ላይ እንዲህ አሉ፦ « ሑሰይን ‘አላህን መውደድ’ በሚባል የዕጣፈንታ ሰይፍ መስእዋት ተደረገ።»

ይህን ቀውል (ንግግር) ሲያብራሩ የሰይድና ሑሰይን መስእዋት ሲኾን በደልን እምቢ ያለበትን ታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ያወሱበታል። ሰይድና ሑሰይን በአላህ መንገድ ላይ እንጂ በዱንያ መንገድ ላይ መስእዋት አልኾኑም። እርሳቸው የትግልን፣ የጽናትን፣ አኺራን የመፈለግ ታላቅ መንፈስ ለኡመት ያሰረጹ ናቸው። ሰይድና ሑሰይን የአላህ ወሊዮች የሚደርሱበት የመጨረሻ የፈናእ ደረጃ የደረሱበት ታላቅ ክስተት እንደነበር ሱፍዮቹ ያብራራሉ።

ኢብን ዐረቢ የሰይድና ሑሰይንን ሞት እንዲህ ያጠቃልሉታል፦ « ወዳጃቸውን (አላህን) ለማግኘት የደረሳቸው የመስእዋትነት ዕጣፈንታ ነው!»

ይህ ታሪክ ሁሌ የሚወሳ ሁሌ የምንደማበት ታሪክ ነው። ድል በ "ማሸነፍ" ውስጥ ብቻ ሳይኾን ታግሎ መቆየት ውስጥ ብቻ እንዳለ የምንማርበት ነው። ትልቁ ማሸነፍ ከፈጣሪ ጋር መገናኘት እንደኾነ የምንማርበትም ነው። ታሪካችንን ስንረዳ በሩ እንዲከፈትልን ሳይኾን በሩ ጋር የመቆምን ክብር እንዲለግሰን በጥልቀት የምንመረምርበት ነው።

ዛሬም በደል አለ፣ ዛሬም ፍትሕ ይኖራል። በየቤቱ በተለያየ ሁኔታ በዳዮችም ተበዳዮችም ልንኾን እንችላለን። በዳይ ኾነን እንደማንቀር ጨካኙን ፈርዖን እናስብ፣ ተበዳዮች በእምባቸውና ጉዳታቸው ተሸንፈው ከመታገል ወደ ኋላ እንዳይሉ ሰይድና ሑሰይን ያስተምሩናል።

በቁስ ወይም ሰዎች አላቸው በሚባሉ ነገሮች አናሳ መኾናችን ከታጋይነት መንፈስ፣ ለእውነት ከመጽናት ሊይዘን አይገባም። ትልቁ ትግል ደግሞ ማለት እውነት ላይ ለመድረስ አላህን ለማግኘት የሚደረገው ነው።

በምድር ላይ ተወዳጆች በኾኑት አህለል በይቶች ላይ የደረሰውን በደልና እዝነት ልቤ ላይ እንዲደርስና በእርሱ እዝነቱ ብርሀን አገኝ ዘንድ አላህን እማጸነዋለሁ።

ሁሉም ምድር ላይ በሐቅና በባጢል ዙሪያ ከርበላ አለ፤ በየዕለቱ ለሚመላለሱብን የበደል ክስተቶች ደግሞ ሁሌም ዓሹራእ አለ።

ያ ከቢርነጂብ ♥

11 months ago | [YT] | 19

Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

ዛሬም ሙሀመድ ፤ ሀቢቡላሂ
ነገም ሙሀመድ፤ ረሱሉላሂ
መቼም ሙሀመድ፤ሸፊኡላሂ

2 years ago | [YT] | 4

Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

Besmela moulid resul
Ashura 1445hijra 2015e.c
Shger 🇪🇹

2 years ago | [YT] | 4

Hadra KebirNejib moulid tube ሀድራ ከቢርነጂብ መውሊድ ቲዩብ

ሰበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትና የአህለሱና ወልጀመአ አሱፊያ ኡለማዎች የሀገር አቀፍ ተወካዮች የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ ።ሐምሌ 10

3 years ago | [YT] | 1